የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Melaku Gedif

October 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከኮንታ ዞን ጭዳ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የደረሰው፡፡

በአደጋው የሁለት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ትናንት ምሽት 12 ሰዓት ላይ በደረሰው አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡