Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሲዳማ ክልል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት የተገነቡ ቤቶች ለነዋሪዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች የተገነቡ 22 መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎቹ ተላልፈዋል፡፡

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የተገነቡት ቤቶቹ በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለነዋሪዎቹ መተላለፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጠቅለይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ደኤታ አቶ መክዩ መሐመድ ፣ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተግኘተዋል፡፡

Exit mobile version