የሀገር ውስጥ ዜና

የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል-የፌደራል ፖሊስ

By Feven Bishaw

October 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ የተከበረው የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት፣ ከቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እና ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመሥራት በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ለአባገዳዎች፣ ለሀደሲንቄዎች፣ ለበዓሉ ታዳሚዎች፣ ለቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እና ለወጣቶች እንዲሁም ለፀጥታና ደኅንነት አካላት የፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡