የሀገር ውስጥ ዜና

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ መሠረታዊ ወታደሮችን አስመረቀ

By amele Demisew

October 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብላቴ የሚገኘው የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው እለት አስመርቋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አለምሸት ደግፌበክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በመርሃ ግብሩ ላይ ታድመዋል።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለውትድርና ሙያ ተመልምለው ስልጠና የወሰዱ መሰረታዊ ወታደሮችም ብቃታቸውን የሚያመላክቱ ወታደራዊ ትርኢቶችን ማሳየታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።