የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

By amele Demisew

October 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ተሸላሚ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዚህም ችግሮችን ተቋቁመው በ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተሸላሚ ይሆናሉ።

ተሸላሚዎቹ በቀጣይ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያነሳሳ የትምህርት ቁሳቁስና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩና ሌሎች እንግዶች ሽልማቱን ከማበርከት በዘለለ የቀጣይ አቅጣጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።