Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች ወደ ሆረ አርሰዲ ሐይቅ እያመሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች ወደ ሆረ አርሰዲ ሐይቅ እያመሩ ነው፡፡

በዓሉ “ኢሬቻ  ለባህላችን ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ከኦሮሚያ ሁሉም  ዞኖች የመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

አሁን ላይም የበዓሉ ታዳሚዎች በአባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች እየተመሩ ወደ ሆረ አርሰዲ ሐይቅ በማቅናት ላይ ናቸው።

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም  እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡

 

Exit mobile version