አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 817 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ከተመለሱት መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ83 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል።