የሀገር ውስጥ ዜና

ጄኔራል አበባው ታደሰ በጎንደር ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን ገበኙ

By Melaku Gedif

October 05, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

በጉብኝቱ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ልዑኩ እየተሠሩ ያሉትን የቅርስ ጥገና እና የመገጭ የውኃ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ተመልክቷል፡፡