አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት እና የብሔረሰቦች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2 የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ የጋራ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባዔው ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በክልሉ ህገመንግስት መሰረት ሁለቱ ምክር ቤቶች የየራሳቸውን የበጀት አመት የመጀመሪያ ስብሰባ ከማድረጋቸው አስቀድሞ ዓመታዊ የጋራ መክፈቻ ያደርጋሉ።
በጉባኤው የ2017 በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት ስራ አቅጣጫ የሚቀርብም ይሆናል።
በአበበች ኬሻሞና በማቱሳላ ማቴዎስ