Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ፡፡

የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በድምቀት ተከብሯል፡፡

ይህን ተከትሎም በዓሉን እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ያደረጉ አካላትን ማመስገናቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በነገው ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ ‘ሆረ ሀርሰዲ’ እንደሚከበር ገልጸው÷ በዓሉ ዕሴቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

Exit mobile version