የሀገር ውስጥ ዜና

በ715 ሚሊየን ብር የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By ዮሐንስ ደርበው

October 05, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ715 ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ዛሬ አስመርቋል።

ፕሮጀክቶቹን የመረቁት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ናቸው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል፣ የክልልና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች መገኘታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ መካከል ባለ 6 ወለል የአሥተዳደር ሕንጻ፣ ባለ 4 ወለል የተማሪዎች ማደሪያ ሕንጻ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች መኖሪያ እና የሕጻናት ማቆያ ሕንጻ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡