የሀገር ውስጥ ዜና

በቆሼ ከተማ ክልል አቀፍ የትምህርት ሴክተር ጉባዔ እየተካሄደ ነው

By Shambel Mihret

October 05, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ክልል አቀፍ የትምህርት ሴክተር ጉባዔውን በቆሼ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፍቃዱ እና የፌደራል እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ እና ከዘርፉ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች በጉባዔው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ተገልጿል፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎን የቢሮውን የ2016 ዓ.ም የሥራ እንቅስቃሴን የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በርዕሰ መሥተዳድሩ ተከፍቷል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው