የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By ዮሐንስ ደርበው

October 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ባስተላለፉት መልዕክትም “ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።