“መላው የኦሮሞ ሕዝብ እንኳን ለ2017 ዓ.ም ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሰህ!!
በሀገራችን የዘመን መለወጥን ተከትሎ ልዩ ልዩ በዓላትን በየዐደባባይ እያከበርን እዚህ ደርሰናል። ከእነዚህ በዓላት መካከል አንዱ በኦሮሞ ሕዝብ በድምቀት የሚከበረውና የማንነቱ መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል አንዱ ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በዐደባባይ የሚያከብረው የኢሬቻ በዓል የሰላምና የአንድነት ምልክት የሆነ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከፈጣሪው ጋር ባለው ቁርኝት የልምላሜ ምንጭ የሆነውን የክረምቱን ዝናብ ለሰጠ ፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ዕለት እንደሆነ ይታወቃል።
ከዚህም በላይ ኢሬቻ አብሮነትና አንድነትን የማጠናከር ኃይል ያለው በዓል ነው። ስለሆነም በዓሉ ለኦሮሞ ሕዝብ የሰላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና በዓል እንዲሆለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።”
– የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት