የሀገር ውስጥ ዜና

ዕሴቶቻችንን በማጎልበት ሀገር የመገንባት ጥረታችንን እናጠናክር- አቶ እንዳሻ ጣሰው

By ዮሐንስ ደርበው

October 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህላዊ ዕሴቶቻችንን በማጎልበት ኢትዮጵያን የመገንባት ጥረታችን አጠናክረን መቐጠል አለብን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል እንከሏን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ብርሃንና ብርታት ምዕራፍ መሸጋገሪያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችህ ብለዋል፡፡

በፌዴራሊዝም ሥርዓቱ ማዕቀፍ ባህላዊ ዕሴቶቻችንን እያጎለበትን ኅብረ-ብሔራዊ አንድነቷ የፀና ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመርነው ጥረት በጋራ ጥረታችን ይሳካል ሲሉም አመላክተዋል፡፡