የሀገር ውስጥ ዜና

የኢሬቻን እሴት መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው- አቶ ጥላሁን ከበደ

By ዮሐንስ ደርበው

October 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻን እሴትና ትውፊት ጠብቆ ለትውልድ ማሻገር የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት÷ ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ትልቅ ቦታ ያለው በአንድነት የሚከበር የምስጋና በዓል ነው ብለዋል፡፡

የሰላምና ይቅርታ፣ የመሻገርና ብሩህ ተስፋ ምልክት የሆነውን ኢሬቻ ከነሙሉ እሴቱና ትውፊቱ ጠብቆ ለትውልድ ማሻገር የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡