የሀገር ውስጥ ዜና

ኢሬቻ አብሮነትን  የሚያጎለብት በዓል ነው- የሐረሪ ክልል

By Mikias Ayele

October 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ አንድነትን፣ አብሮነትን እና መተባበርን የሚያጎለብት በዓል መሆኑን የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ገለጸ፡፡

የክልሉ መንግሥት የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት÷ ኢሬቻ ከክረምት ወደ በጋ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን በማሰብ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ የሚከበር የዐደባባይ በዓል ነው ብሏል።

ኢሬቻ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር÷ አንድነትን፣ አብሮነትን እና መተባበርን የሚያጎለብት በዓል መሆኑንም ገልጿል፡፡

በዓሉ የሕዝቦችን ትስስር የሚያጠናክር እና የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን የሚያሳድግ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡