Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከ6 ሠዓት ጀምሮ እስከ የፊታችን ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከልሉን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ክልከላው የተላለፈው ለኢሬቻ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደኅንነትን ለማስጠበቅ መሆኑን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊሶችም አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡

Exit mobile version