ስፓርት

ኪሊያን ምባፔ በጉዳት ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆነ

By Melaku Gedif

October 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ በጥቅምት ወር ከእስራኤልና ቤልጂየም ጋር ለምታደርጋቸው የአውሮፓ ሀገራት ጨዋታዎች ኪሊያን ምባፔን በስብስቧ ውስጥ አላካተተችም፡፡

በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾው ቡድኑ በወሩ ለሚኖሩት ሁለት ጨዋታዎች የሚካተቱ ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

በዝርዝሩ ኪሊያን ምባፔ በጉዳት ምክንያት ያልተካተተ መሆኑም ተነግሯል።

ተጫዋቹ ጉዳት ያስተናገደው በስፔን ላሊጋ ለክለቡ ሪያል ማድሪድ ሲጫወት መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾው የባየርን ሙኒኩን ሚካኤል ኦሊሴ በስብስባቸው ማካተታቸው ተነግሯል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የነበረው አንቷን ግሬዝማን እራሱን ከብሄራዊ ቡድኑ ማግለሉ ይታወሳል ሲል ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡