ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

By Shambel Mihret

October 03, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማ በድሬደዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ጎሎችን ኪቲካ ጅማ፣ አንደኛዋን ጎል ደግሞ ፉዓድ ፈረጃ ሲያስቆጥር የአርባምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል አህብያ ብራያን አስቆጥሯል፡፡