አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ህብረት ሰብሳቢ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ በተሻለ መልኩ ስለሚሳተፉበት ሁኔታና ስለሚኖራቸው ሚና ሀሳቦች ተነስተው መግባባት ላይ መደረሱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን÷ የዛሬው ውይይትም ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡