Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመቐለ በ9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቐለ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ በ9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ሊሰሩ በታቀዱ የልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከነዋሪዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሯል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ይትባረክ አምሀ በበጀት ዓመቱ በ9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ለማካሄድ መታቀዱን ተናግረዋል።

በተለይም ለትምህርትና ጤና ተቋማት ማስፋፋትና ጥገና ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው÷ባለፈው ዓመት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የእቅዱ አካል እንደሆኑ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version