አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ”ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በበዓሉ አከባበር ስነስርዓት አባ ገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዓሉን አስመልክቶ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ ባሕላዊ ምግቦች ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የኢሬቻ ሳምንትን ምክንያት በማድረግም የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን አባገዳዎች የምርቃት ስነ ስርዓት ማከናወናቸውን ከክፍለከተሞቹ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።