Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሎጂስቲክስ ዘርፉን ዓለም ወደ ደረሰበት አሰራር ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን በታቀደው ልክ በመተግበር ሀገራዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሎጂስቲክስ እና የባቡር ሎጂስቲክ ዘርፉን ዓለም ወደ ደረሰበት አሰራር ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በኢትዮጵያ የባቡር እና የሎጂስቲክስ ዘርፎች ሪፎርም ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)÷ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን በታቀደው ልክ በመተግበር ሀገራዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሎጂስቲክስ እና የባቡር ሎጂስቲክ ዘርፉን ዓለም ወደ ደረሰበት አሰራር ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በባቡር እና በሎጂስቲክስ ሴክተሮች የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን የተመለከተ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በለይኩን ዓለም

Exit mobile version