አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የፎረንሲክ ሳይንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ዛሬ የኢንስቲትዩቱን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላም ኢንስቲትዩቱን በሚመለከት እንዲሁም ከምርቃት አስቀድሞ መካተትና መሟላት ባለባቸው ግብዓቶች ላይ ምክክር መደረጉን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የሚታዩ የወንጀል ድርጊቶችን መከላከልና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መመርመር ያስችለው ዘንድ ኢንስቲትዩቱን መገንባቱ ተገልጿል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የወንጀል ምርመራ ሂደትን ከማቅለል ባሻገር ቀልጣፋና ዘመኑን የሚመጥን የወንጀል ምርመራ እንዲሁም የማስተማሪያ ተቋም ሆኖ መገንባቱ ተጠቅሷል፡፡