Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጅቡቲን 5 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ ጋር ያደረገውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሁለተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከጅቡቲ አቻው ጋር አድርጓል፡፡

ይህን ጨዋታም ቸርነት መንግሥቱ (2)፣ ናትናኤል ሰለሞን፣ ዳግም አወቀ እና ሰለሞን ገመቹ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተጋጣሚውን 5 ለ 0 ማሸነፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

 

 

Exit mobile version