ስፓርት

የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጠኝ አሊዩ ሲሴን አሰናበተ

By ዮሐንስ ደርበው

October 02, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አመታት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጠኝ የነበረው አሊዩ ሲሴ መሰናበቱ ተነገረ።

የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስልጣኙ ኮንትራት በማለቁ ማሰነበቱን በመግለጽ አሰልጣኙ በብሔራዊ ቡድኑ ጋር ለነበረው ስኬት አመስግኗል፡፡

የ48 ዓመቱ አሊዩ ሲሴ በአሰልጣኝነት ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳ ነው።