Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቃለች፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ትርምስ በእጅጉ አሳሳቢ ነው ብሏል።

ቤጂንግ ግጭቱን የሚያራግቡ እና ውጥረቶችን የሚያባብሱ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙም ጠይቃለች።

ቻይና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ተፅዕኖ ያላቸው ሀገራት ገንቢ ሚና እንዲጫወቱም ነው ያሳሰበችው።

በጋዛ የተራዘመው ጦርነትም የአሁኑ የመካከለኛው ምስራቅ ትርምስ መንስኤ ነው ብላ እንደምታምን ተገልጿል፡፡

በዚህም ሁሉም ወገኖች ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በአፋጣኝ መስራት አለባቸው ብሏል መግለጫው።

በአፈወርቅ እያዩ

Exit mobile version