የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ እንዳሻው ጣሰው ከመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና ጄኔራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና ጄኔራል መኮንኖች ጋር በጽህፈት ቤታቸዉ ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ አሁናዊውን ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታ መገምገም እና የፀጥታ ሁኔታዉ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ ላይ የክልሉ ፀጥታና ሠላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ካሳን ጨምሮ ሌሎችም የቢሮዉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡