አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤል ማስወንጨፍ መጀመሯን የእስራኤል መከላከያ ሃይል አስታወቀ፡፡
የሚሳኤል ጥቃቶቹ ወደ እስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ ያነጣጠሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎም የቴላቪቭ ነዋሪዎች የአደጋ ማስጠንቀቂያ ሲሰሙ ደህንነታቸው ወደ ሚጠበቅ ቦታ በፍጥነት እንዲሄዱ የሀገሪቱ መከላከያ ሀይል ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል::