የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በካርቱም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘች

By Feven Bishaw

October 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እንደምታወግዝ አስታውቃለች፡፡

የኢትዮጵያ በሱዳን ያሉ ሁሉም ወገኖች አለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ደንቦችን እንዲያከብሩ እና የዲፕሎማቲክ ሰራተኞችን እና ተቋማትን አደጋ ላይ ከሚጥል ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርባለች፡፡