Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጀርመን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የጀርመን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሄኮ ኒትዝሺከን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በጋራ ፍላጎቶች ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ወቅት÷ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እየተጫወተችው ያለውን ቁልፍ ሚና አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

እንዲሁም ከሌሎች አካላት ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ በማሳደግ በአፍሪካ ቀንድ ልማት፣ ደኀንነት እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያደገ መምጣቱን ሚኒስትር ዴኤታው ማድነቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የጀርመን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሄኮ ኒትዝሺከ በበኩላቸው÷ የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ የሚሆነው ቀጣናዊ አንድነት ሲጠናከር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለቀጣናው ደኅንነት መረጋገጥ የኢትዮጵያ ሚና ወሳኝ መሆኑንም በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

Exit mobile version