የሀገር ውስጥ ዜና

ኢሬቻ የሀገርን ገጽታ በሚገነባ መልኩ እንዲከበር ሚናችንን እንወጣለን- ወጣቶች

By amele Demisew

October 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል ትውፊቱን ጠብቆ የሀገርን ገጽታ በሚገነባ መልኩ እንዲከበር ሚናችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተሞች ወጣቶች ተናገሩ።

ወጣቶች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የኢሬቻ በዓል ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተሰባስበው የሚያከብሩት የጋራ በዓል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበርም የሚጠበቅብንን ሚና እናበረክታለን ብለዋል፡፡

ኢሬቻ አንድነትና አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ቱሪስቶችን በመሳብ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው÷ ከዚህ አንጻር ሁሉም እንግዶችን በአግባቡ ተቀብሎ በማስተናገድ ረገድ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

በዓሉ ኢትዮጵያ ያላትን ባህልና እሴት አጉልቶ ለማሳየትና ለማስተዋወቅ የሚያስችል ትልቅ ሁነት እንደሆነም አንስተዋል፡፡