የሀገር ውስጥ ዜና

የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሄቦ በዓል እየተከበረ ነው

By amele Demisew

October 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ‘ሄቦ’ በዓል በሳጃ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ሄቦ ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሸጋገሪያ በዓል መሆኑ ተገልጿል።

የሄቦ በዓል የአዲስ ዓመት ብርሃን ማብሰሪያ፣ በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው ርቀው የሚኖሩ ከቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ታላቅ ክብረ በዓል እንደሆነ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ ተናግረዋል።

ሄቦ “የየም ብሔረሰብ አሮጌውን ዘመን ሸኝቶ ወደ አዲስ ዘመን፣ ወደ ቀጣይ አዲስ ምዕራፍ የሚሸጋገርበትና እሴቱን ወደ ቀጣዩ ትውልድ በክብር በማስተላለፍ፣ ብሩህ ተስፋን ሰንቆ ነገን የተሻለ ለማድረግ ትጋትንና መነሳሳትን የሚፈጥርበት እንደሆነ ተገልጿል።

በወርቃፈራሁ ያለው