Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሻምፒየንስ ሊጉ አርሰናል ከፒኤስጂ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ አርሰናል በሜዳው ከፈረንሳዩ ፒኢስጂ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ በሬድ ቡል አሬና የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ ከፈረንሳዩ ብረስት እንዲሁም የጀርመኑ ስቱትጋርት ከቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ ይጫወታሉ፡፡

በሌላ ጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 4 ሠዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም አርሰናል ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

በፒኤሲጂ በኩል ፈረንሳዊው ኦስማን ደምቤሌ ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ባርሴሎና ከስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ፣ የጀርመኑ ባየርሊቨርኩሰን ከኤሲሚላን፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከስኮትላንዱ ሴልቲክ፣ ኢንተርሚላን ከሰርቢያው ሬድ ስታር ቤልግሬድ ይጫወታሉ፡፡

በተጨማሪም የኔዘርላንዱ ፒኢስቪ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን እንዲሁም የስሎቫኪያው ስሎቫን ብራቲስላቫ ከማንቼስተር ሲቲ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን  ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version