የሀገር ውስጥ ዜና

ለለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ግብዓት የሚያጓጉዙ 36 ዘመናዊ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ለሚ ደረሱ

By ዮሐንስ ደርበው

October 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደሀገር ውስጥ እያስገባቸው ከሚገኙ 330 ገልባጭ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል 36 ያህሉ ሳይት መድረሳቸው ተገለጸ፡፡

ተሽከርካሪዎቹ የሲሚንቶ ምርት ግብዓት ማዕድን ከማምረቻ ጣቢያ ወደ ማከማቻ ቦታ የሚያጓጉዙ መሆናቸውን የፋብሪካው መረጃ አመላክቷል፡፡

ማዕድኑ የሚመረተው በጀማ ወንዝ ሸለቆ በመሆኑና የመልክዓ-ምድሩን አስቸጋሪነት በመረዳት እነዚህን ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ለመግዛት ከፍተኛ ዋጋ መከፈሉን ፋብሪካው አስታውቋል፡፡

በቀን 150 ሺህ ኩንታል የማምረት አቅም ያለው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር ” ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የመንግሥታችን በፍጥነት፣ በግዝፈት እና በንፅህና የመገንባት ጽኑ አቋም ማሳያ ነው” ማለታቸው ይታወቃል፡፡