ስፓርት

ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ ቅጣት ተላለፈበት

By Mikias Ayele

September 30, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ዲሲፕሊን ኮሚቴ በካሜሩን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኤቶ ላይ ቅጣት መጣሉን አስታውቋል፡፡

የቀደሞ የባርሴሎና እና ኢንተርሚላን ኮከብ ቅጣት የተላለፈበት ያልተገባ ባህሪ በማሳየቱ እና የፊፋን ፍትሃዊ የጨዋታ መርሆች በመጣሱ ነው ተብሏል፡፡

ኤቶ ድርጊቱን የፈጸመው በኮሎምቢያ ቦጎታ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ዓለም ዋንጫ ብራዚል ከካሜሮን ባደረጉት ጨዋታ ወቅት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ኤቶ ለ6 ወራት ያህል የካሜሮን የሴቶች እና ወንዶች ብሄራዊ ቡድኖች በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች እንዳይሳተፍ መታገዱን ፊፋ አስታውቋል፡፡