Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

6ኛው የኮሜሳ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ንግድ ትርዒት በኢትዮጵያ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

21 የኮሜሳ አባል ሀገራትን የሚያሳትፈው 6ኛው የኮሜሳ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒት በፈረንጆቹ 2025 ግንቦት ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኮሜሳ ስር የሚገኘውና በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ፌዴሬሽን ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የንግድ ትርዒቱ ለኢትዮጵያውያን ሴት የሥራ ፈጣሪዎች መነቃቃት የሚፈጥርና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ ተወካዮች በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ሰፊ የቆዳ ስፋትና ህዝብ ቁጥር ባለቤት እንደመሆኗ የንግድ ትርዒቱ አዳዲስና ሰፊ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመጠቀም እንደሚረዳት ገልጸዋል፡፡

በንግድ ትርኢቱ ላይ ከ500 በላይ ሥራ ፈጣሪ ሴቶች ሥራዎቻቸውንና ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተወካዮቹ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

Exit mobile version