አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አቅራቢያ ለሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ የሚደረገውን ዝግጅት ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመምከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩ ቦታውን ለግንባታ ዝግጁ ለማድረግ ከተደራጀ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር የመስክ ምልከታ በማድረግ ምክክር ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡
በ120 ሔክታር መሬት ላይ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያው በቅርቡ ግንባታው እንደሚጀመር መገለፁን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡