Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን አፈጻጸም ገመገሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ገምግመዋል፡፡

ከንቲባዋ ባለፉት ሁለት ቀናት በኮሪደር ልማት ስራ የተጀመሩ የታክሲ እና አውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች እንዲሁም የፒያሳ መልሶ ማልማት ስራዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው መገምገማቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በዚህም በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ ቸርችል መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፣ ባሻ ወልዴ፣ ደጎል አደባባይ፣ ቦሌ ድልድይ፣ ቦሌ መንገድ ደንበል፣ ሳር ቤት፣ ቀበና፣ መገናኛ እና ሲኤምሲ አካባቢዎች ከመሬት በታች ከ 2 እስከ 3 ወለል ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ የሆኑ የታክሲና የአውቶቡስ ተርሚናሎች የግንባታ ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

ግንባታዎቹ በታቀደው ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉም አረጋግጠዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራው የዋና መንገድ አካባቢን ብቻ ሳይሆን የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ጨምሮ ከተማዋን ለመኖሪያ ምቹ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ የተጀመሩ መሰረተ ልማቶችንም የሚያካትት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

 

Exit mobile version