የሀገር ውስጥ ዜና

የኢሬቻ 2017 ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ

By Melaku Gedif

September 30, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ 2017 ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።

በሀገሬ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን ተዘጋጅቶ ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው ኢሬቻ 2017 ኤክስፖ የፓናል ውይይት፣ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ ባዛርና የተለያዩ ሁነቶች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።

ኤክስፖው የባህል ልውውጥ፣ ወዳጅ ዘመድ የሚገናኝበትና የሚዝናናባት እንዲሁም የባህል አልባሳትን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበት መሆኑ ተነግሯል።