ስፓርት

አንቶዋን ግሬዝማን ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች እራሱን አገለለ

By Melaku Gedif

September 30, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው ተጫዋች አንቶዋን ግሬዝማን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቆሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ተጫዋቹ ከብሔራዊ ቡድኑ መለየቱን በመግለጽ በቀሪ የእግር ኳስ ሕይወቱ ለክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ትኩረት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በፈረንጆቹ ከ2014 ጀምሮ ለሀገሩ ፈረንሳይ መጫወት የጀመረው ግሬዝማን ዓለም ዋንጫን ጨምሮ የተለያዩ ድሎችን አጣጥሟል።

ለብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው ጨዋታዎችም 44 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በነበረው ስኬታማ ቆይታ ድጋፍ ላደረጉለት ሁሉ ምስጋና ማቅረቡን ዘገባዎች አመልክተዋል።