አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት እየለማ ያለ ሰብልን ጎብኝተዋል፡፡
በመስክ ምልከታ መርሐ ግብሩ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ በጉራጌ ዞን በግብርና ኢንቨስትመንት ተሰማርተው የበቆሎ ምርጥ ዘር፣የቅባት እህሎች እና ሌሎች የልማት ስራዎችን መመልከታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡