አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮደርስ ስልጠና ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ አሻድሊ÷የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ሥልጠና የዲጂታል ኢትዮጵያን ስኬት እውን ለማድረግ የተያዘውን ጥረት ለማሳካት ያስችላል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ዜጎች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማዳበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚስችል አስገንዝበዋል፡፡
ስልጠናው የዲጂታል ኢኮኖሚውን በዳበረ የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት የሚመራ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል፡፡
ስለሆነም የክልሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የመንግስት ተቋማት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ስልጠናውን ወስደው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ጥረት እንዲደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡