Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የኮሪደር ልማት ሥራን ለማጠናከር የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራን በክልሉ ሁሉም ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት÷ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የኮሪደር ልማት ሥራን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የተሻለ ከተማ ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ እየተደረገ ላለው ሒደት የኮሪደር ልማት ስራ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል፡፡

ለዚህም የከተማ ነዋሪዎች እና የሥራ አመራሩ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

በመድረኩ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version