Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ 125 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ ጣለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የሀገሪቱን አየር ክልል ጥሰው የገቡ 125 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏን ገልጻለች፡፡

ጥቃት ለማድረስ የአየር ክልል ጥሰው የገቡ 125 ዩኤቭ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በተሰካ ሁኔታ ማምከን መቻሉን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

67 ድሮኖች በደቡባዊ ሩሲያ መምከናቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪ አንድሪይ ቦቻሮቭ የተናገሩ ሲሆን÷ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን አመልክተዋል፡፡

ሌሎች 17 ድሮኖች በቤልጎርድ አካባቢ ተመተው ሲወድቁ 17 ድሮኖች ደግሞ በቮሮንዥ መውደማቸውን የአካባቢዎቹ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

አብዘኞዎቹ ድሮኖች በቮሮኔዥ ከተማ ተመትተው የወደቁ ሲሆን÷ሁለት የመኖሪያ ሕንጻዎች ከመቃጠላቸው በቀር የከፋ ጉዳት አለማድረሳቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሩሲያ ለጥቃት ወደ ሀገሯ የሚሰነዘሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እያመከነች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version