Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለሃብቶች በክልሉ ኢንቨስት በማድረግ ኢኮኖሚን ለማሻሻል መስራት አለባቸው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት ኢኮኖሚን ለማሻሻል መስራት አለባቸው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በአርባምንጭ ከተማ በግል ባለሃብት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን ሆቴል መርቀው ከፍተዋል፡፡

አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት ኢኮኖሚን ለማሳደግ ጉልህ አስትዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ክልሉ የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት መሆኑን አውስተው÷ ያሉትን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም ለሀገሪቱ ተጨማሪ ሃብት ማመንጨት ይገባል ነው ያሉት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተቋማትን አገልግሎት ማዘመን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በመደጋገፍ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ አለብን ሲሉ አጽንኦት መስጠታቸውንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version