አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡና ምርታማነትና ጥራት ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም ከምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት በንቅናቄ መድረኩ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
በመድረኩም የቡና ምርታማነትን በሚያሳድጉና ጥራት በሚጨምሩ ተግባራት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የውይይቱ ተሳታፊዎች ከውይይቱ ጎን ለጎን የቀረበውን የቡና ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል፡፡
በደሳለኝ አበራ