Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ መርሐ-ግርብ ሲቀጥል ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚሁ መሠረት 10 ሠዓት ላይ ኢፕስዊች ታውን በሜዳው አስቶን ቪላን የሚያስተናግድ ሲሆን÷ አስቶንቪላ የማሸነፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ በቅድመ-ጨዋታ ግምት እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በዛሬው የመጨረሻ ጨዋታ መርሐ-ግብር 12 ሠዓት ከ30 ላይ በኦልድ ትራፎርድ የሚደረገው የማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ምንም እንኳን ቀያይ ሰይጣኖቹ እንደሚያሸንፉ ቢገለጽም ከቶተንሃም ብርቱ ፈተና ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ሊቨርፑል በፕሪሚየር ሊጉ አናት ላይ ሲቀመጥ÷ አስቶንቪላ 5ኛ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር 9ኛ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ 11ኛ እንዲሁም ኢፕስዊች ታውን 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Exit mobile version