Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተመድ ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ የተደረገው በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው፡፡

በውይይታቸውም በወቅታዊ ቀጣዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ መሠረት በቀጣናው ውጥረትን በማርገብ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ በውይይታቸው ላይ ተነስቷል፡፡

Exit mobile version